OJP Logo

Office of Justice Programs

A Division of the Minnesota Department of Public Safety
 

Victim Information - Amharic

ለሁሉም የወንጀልተጎጂዎች የሚሰጡ መብቶችና አገልግሎቶች 


በአመጽ የወንጀል ድርጊት የተነሳ ለሚደርሱብዎ ኪሳራዎች የፋይናንስ/የገንዘብ እርዳታ ለማግኘት የማመልከት መብት አሉዎ። ይህ እርዳታ የንብረት ኪሳራን አያጠቃልልም። ለማመልከቻና መረጃ ለማግኘት በስልክ ቁጥር 651-201-7300 ይደውሉ። Twin Cities ውጭ በሚከተለው ስልክ ቁጥር ይደውሉ፡  888-622-8799 ወይም ወደ OJP ድረገጽ: ojp.dps.mn.gov. ይግቡ። TTY: 651-205-4827

 

አስፈጻሚ ድርጅቱ የእርስዎን ማንነት የሚገልጽ መረጃን ለህዝብ ይፋ ከመሆን እንዲያግድ የመጠየቅ መብት አሉዎት። የህግ አስፈጻሚ ድርጅቱ ይህ የሚቻል ስለመሆኑ ይወስናል።

 

ፈጻሚው ክስ ተመስርቶበት ከሆነ ካሳ (ጥፋት ፈጻሚ እንዲከፍል በፍርድ ቤት የሚታዘዝና ለተጎጂ የሚከፈል ገንዘብ) የመጠየቅ መብትን ጨምሮ ስለ ምርመራ ሂደቱ መረጃ የማግኘት እና በምርመራ ሂደቱ ላይ የመሳተፍ መብት አሉዎት።

 

እንደ ተጎጂ መብቶችዎ እንደተጣሱ የሚሰማዎ ከሆነ፣ ወይም እዚህ ላይ ስለሚቀርቡ መብቶችዎ ወይም መረጃዎች ካልተረዱ የወንጀል ተጎጂ ፍትህ ክፍልን / Crime Victim Justice Unit/ በስልክ ቁጥር 651-201-7310, 800-247-0390 ወይም cvju.ojp@state.mn.us ያነጋግሩ።

 የቤት ውስጥ ጥቃት ተጎጂዎች መብቶች 


የወንጀል አቤቱታ ለማስመዝገብ የከተማው ወይም ካውንቲውን ጠበቃ መጠየቅ ይችላሉ።

 

በተጨማሪም ወደ ፍርድ ቤት የመሄድና ከቤት ውስጥ ጥቃት የመጠበቅ ትእዛዝ እንዲሰጥልዎ በመጠየቅ አቤቱታ የማስመዝገብ መብት አሉዎ። ትዕዛዙ የሚከተሉትን ያጠቃልላል:

 

  • ጥቃት ፈጻሚውን ተጨማሪ የጥቃት ድርጊቶች ከመፈጸም የሚያቅብ ትእዛዝ;
  • ጥቃት ፈጻሚውን መኖሪያ ቤትዎን ለቆ እንዲሄድ የሚያዝ ትዕዛዝ;
  • ጥቃት ፈጻሚውን ወደ መኖሪያ ቤትዎ (ወይም በመኖሪያ ቤትዎ ዙሪያ የሚገኝ አሳማኝነት ያለው ቦታ) ትምህርት ቤት፣ የስራ ቦታ ወይም የስራ ቅጥር ቦታ እንዳይገባ የሚከለክል ትዕዛዝ;
  • ለእርስዎ ወይም ለሌላኛው ወላጅ ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጅዎ ወይም ልጆችዎን እንድትንከባከቡ እና/ወይም እንድትጠይቁ የሚወስን ትዕዛዝ፣ ወይም
  • ጥቃት ፈጻሚው ይህን እንዲያደርግ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ከተሰጠው ለእርስዎና ለአካለ መጠን ላልደረሱ ልጆችዎ የገንዘብ ድጋፍ እንዲከፍል የሚያዝ ትዕዛዝ።

 

በተጨማሪም በጉዳዩ ላይ የተመሰረተው ክስ ተቀባይነት ካላገኘ ወይም የወንጀል ክሶቹ ከተሰረዙ ይህን በተመለከተ ማስታወቂያ የማግኘት መብት አሉዎ።

 

 

ስለ ጥበቃ ትዕዛዞች ወይም ከትንኮሳ የመታቀብ ትዕዛዞች በተመለከተ በአካባቢዎ ድጋፍ ስለሚያገኙበት ሁኔታ እርዳታ ለማግኘት የሚከተለውን ያነጋግሩ፡

 

የሚኔሶታ የቀን አንድ የቀውስ መስመር/ Minnesota Day One Crisis Line: በስልክ ቁጥር 866-223-1111 ይደውሉ ወይም 612-399-9995 የጽሁፍ መልዕክት ይላኩ። ድረገጽ ለማግኘት እዚህ ላይ ይጫኑ። 

እርዳታ ለማግኘት

ርዳታ ለማግኘት እዚህ ላይ ይጫኑ፣ ወይም የአካባቢዎን የህግ አስፈጻሚ ድርጅት ያነጋግሩ።


 

ስለ ሕግ ማስፈፀም የተመለከተ የህግ ማስታወቂያ መስፈርቶች

የህግ አስፈጻሚ ኦፊሰሮች ከሁሉም የወንጀል ተጎጂዎች ጋር በሚያደርጉት የመጀመሪያ ግንኙነት ስለ መብቶችና የመረጃ ምንጮች የተመለከተ የመጀመሪያ ማስታወቂያ ስጠት አለባቸው። የሚኔሶታ ሕጎች ክፍል 611A.02, ንዑስ ክፍል 2(b)/Minnesota Statutes section 611A.02,።

የህግ አስፈጻሚ ኦፊሰሮች በመጀመሪያ ማስታወቂያው ላይ ለሁሉም የቤት ውስጥ ጥቃት ተጎጂዎች ተጨማሪ መረጃ መስጠት አለባቸው። የሚኔሶታ የሕጎች ክፍል/ Minnesota Statutes section 629.341, subd. 3.