Victim information in Amharic
ለሁሉም የወንጀል ሰለባዎች ተደራሽ የሆኑ መብቶችና አገልግሎቶች
- በአመጽ ወንጀል ምክንያት ለደረሰ ኪሳራ ለወንጀል ሰለባዎች ማካካሻ ፕሮግራም የገንዘብ እርዳታ የማመልከት መብት አልዎት፡፡ ይህ እርዳታ የንብረት ኪሳራን የሚሸፍን አይሆንም፡፡ ለማመልከትና መረጃ፣ በ 651-201-7300 ወይም 888-622-8799 ይደውሉ ወይም ወደ የፍትህ ፕሮግራሞች ጽህፈት ቤት ድረገጽ ይሂዱ፡ ojp.dps.mn.gov
- የህግ አስከባሪ ኤጀንሲ ማንነትዎን የሚገልጽ መረጃን የህዝብ መዳረሻ ላይ ክልከላ እንዲያደርግ የመጠየቅ መብት አልዎት፡፡ ይህ የሚቻል ከሆነም የሕግ አስከባሪው ኤጀንሲ የሚወስነው ጉዳይ ይወስናል፡፡
- አንድ ወንጀለኛ ከተከሰሰ ይህን የማወቅ፣ በክስ ሂደት ውስጥ የመሳተፍና ካሳን የመጠየቅ መብት አለዎት፡፡
እንደ ተጎጂ መብቶችዎ እንደተጣሱ የሚሰማዎ ከሆነ፣ ወይም እዚህ ላይ ስለሚቀርቡ መብቶችዎ ወይም መረጃዎች ካልተረዱ የወንጀል ተጎጂ ፍትህ ክፍልን / Crime Victim Justice Unit/ በስልክ ቁጥር 651-201-7310, 800-247-0390 ወይም cvju.ojp@state.mn.us ያነጋግሩ።
የቤት ውስጥ ጥቃት ሰለባዎች ያሏቸው መብቶች
የወንጀል አቤቱታ ለማስመዝገብ የከተማው ወይም ካውንቲውን ጠበቃ መጠየቅ ይችላሉ።
በተጨማሪም ወደ ፍርድ ቤት የመሄድና ከቤት ውስጥ ጥቃት የመጠበቅ ትእዛዝ እንዲሰጥልዎ በመጠየቅ አቤቱታ የማስመዝገብ መብት አሉዎ። ትዕዛዙ የሚከተሉትን ያጠቃልላል:
- የቤት ውስጥ ጥቃት ሰለባ ከሆኑ የጥበቃ ትእዛዝ እንዲሰጥዎ ለፍርድ ቤት አቤቱታ ማቅረብና ለቤት ውስጥ ጥቃት ተጠያቂ የሆነውን ግለሰብ ተጠያቂ ማድረግ ይችላሉ፡
ከተጨማሪ ጥቃት መጠበቅ፣ - ከቤትዎ ለቆ ማስወጣት፣
- ከመኖሪያዎ፣ ከትምህርት ቤትዎ፣ ከንግድ ስራዎ ወይም ከስራ ቦታዎ እንዲርቅ ማድረግ፣ እና
- ግለሰቡ በህጋዊ መንገድ ይህን የማድረግ ግዴታ ካለበት ለርስዎና ለአካለ መጠን ላልደረሰ ልጅ የገንዘብ ድጋፍ እንዲፈጽም ማድረግ፡፡
በተጨማሪም በጉዳዩ ላይ የተመሰረተው ክስ ተቀባይነት ካላገኘ ወይም የወንጀል ክሶቹ ከተሰረዙ ይህን በተመለከተ ማስታወቂያ የማግኘት መብት አሉዎ።
ስለ ጥበቃ ትዕዛዞች ወይም ከትንኮሳ የመታቀብ ትዕዛዞች በተመለከተ በአካባቢዎ ድጋፍ ስለሚያገኙበት ሁኔታ እርዳታ ለማግኘት የሚከተለውን ያነጋግሩ፡
የሚኔሶታ የቀን አንድ የቀውስ መስመር/ Minnesota Day One Crisis Line: በስልክ ቁጥር 866-223-1111 ይደውሉ ወይም በ612-399-9995 የጽሁፍ መልዕክት ይላኩ። እዚህ ላይ ይጫኑ።
እርዳታ ለማግኘት
እርዳታ ለማግኘት እዚህ ላይ ይጫኑ፣ ወይም የአካባቢዎን የህግ አስፈጻሚ ድርጅት ያነጋግሩ።
ስለ ሕግ ማስፈፀም የተመለከተ የህግ ማስታወቂያ መስፈርቶች
የህግ አስፈጻሚ ኦፊሰሮች ከሁሉም የወንጀል ተጎጂዎች ጋር በሚያደርጉት የመጀመሪያ ግንኙነት ስለ መብቶችና የመረጃ ምንጮችን የተመለከተ የመጀመሪያ ማስታወቂያ መስጠት አለባቸው። የሚኔሶታ ሕጎች ክፍል 611A.02, ንዑስ ክፍል 2(b)/Minnesota Statutes section 611A.02,።
የህግ አስፈጻሚ ኦፊሰሮች በመጀመሪያ ማስታወቂያው ላይ ለሁሉም የቤት ውስጥ ጥቃት ተጎጂዎች ተጨማሪ መረጃ መስጠት አለባቸው። የሚኔሶታ የሕጎች ክፍል/ Minnesota Statutes section 629.341, subd. 3.
